ከፍተኛ ጉዳት ፈፃሚ ሄሊኮፕተሮች
የጦር ሄሊኮፕተሮች በተለምዶ መትረየስ፣ ሮኬቶች እና ፀረ ታንክ ሚሳኤሎች የታጠቁ ናቸው። የአሜሪካ Apache በተለምዶ AGM-114 Hellfire ሚሳኤልን በዚህ ሚና ይይዛል። የጦር ሄሊኮፕተሮች በየትኛውም ዘመናዊ ወታደራዊ ትጥቅ ውስጥ ካሉ በጣም ኃይለኛ የማጥቃት አቅም ይፈጥርላቸዋል።
እነዚህ ከፍተኛ ጥቃት ፈፃሚ ሄሊኮፕተሮች የተለያዩ የጦር መሣሪያዎችን ጠምደው ከምድር በቅርብ ርቀት በማስወንጨፍ ኢላማቸውን የሚመቱ ናቸው:: የጦር ሄሊኮፕተሮች በጠላት እግረኛ ፣ ምሽግ ፣ ታንኮች ወዘተ ላይ ከፍ ያለ ጉዳት ማድረስን ታላሚ አድርገው የተሠሩ ናቸው:: ጥቃት ሰንዛሪ ሄሊኮፕተሮች መትረየስ፣ ሮኬቶች፣ ፀረ ታንክ ሚሳኤል ተጠምዶባቸወም ለግዳጅ ይሰማራሉ::
ዛሬ በዓለም ላይ በአገልግሎት ላይ ካሉት በጣም ኃይለኛ የጥቃት ሄሊኮፕተሮች ጥቂቶቹ እዚህ አሉ። በዓለም ላይ እስካሁን ምርጥ በማጥቃት አቅማቸው ቀዳሚዎች የሆኑትን የጦር ሄሊኮፕተሮች እንመልከት፤
የመረጃ ምንጫችን- (https://www.hotcars.com/most-powerful-military-helicopters/)
5ኛ- የሄሊኮፕተሩ መጠሪያ - ሚልሚ - 28
የተሰራው በራሽያኖች ሲሆን ይህ ሩሲያ ሠራሹ ሚልሚ-28 ሄሊኮፕተር በሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ሀገራት ሀቮክ
በሚል ቅጽል ይታወቃል:: የሄሊኮፕተሩ ንድፍ ቀንም ሆነ ሌሊት በማንኛውም የአየር ንብረት
እንዲያገለግል ተደርጐ የተሠራ ነዉ:: የሄሊኮፕተሩ የመጀመሪያ በረራ የተካሄደዉ
እ.ኤ.አ. በ1982
ነበር:: በሩሲያ ጦር ውስጥ ደግሞ
በግዳጅ ስምሪት የዋለው እ.ኤ.አ በ 2009 ላይ ነው:: በግዳጅ ስምሪት ሩሲያ ሄሊኮፕተሩን በጦር ኀይሏ ውስጥ በሶሪያ አሰማርተውም ነበር::
4ኛ- የሄሊኮፕተሩ መጠሪያ - ካሞቭካ-50
የተሰራው
በራሽያኖች ሲሆን ካሞቭካ - 50 ወይም “ብላክሻርክ” በሚል
ቅጽል ስም የሚጠራው ሄሊኮፕተር
ሲሆን የንድፍ ሥራው እ.አ.አ በ1982
ተጠናቆ ሙሉ በሙሉ ተመርቶ ለጦር ኀይል አገልግሎት የበቃው ደግሞ 1995 እ.ኤ.አ ነው:: ሄሊኮፕተሩ አንድ ሰው ብቻ የሚይዝ
መቀመጫ ያለው ነዉ:: ካሞቭ ሄሊኮፕተር በሂደት ሥሪቱን አሻሽሎም ካሞቭ ሁለት
በሚል ተመርቷል:: ሄሊኮፕተሩ ሩሲያ በሶሪያ ባካሄደችው ዘመቻ አገልገሎት ላይ ውሏል::
3ኛ - የሄሊኮፕተሩ መጠሪያ ሀርቢን “Z”፣ “WZ-19”
የተሰራው-በ ቻይኖች ሲሆን ሀርቢን “Z” ወይም “WZ-19” በጦር ኀይል ውስጥ አገልግሎት ላይ የዋለው በ2012 እ.ኤ.አ ነው:: ሄሊኮፕተሩ በግራ ቀኝ ጐኑ በሚይዛቸው የላቁ አጥቂ መሣሪያዎች ምክንያት ተመራጭ ሆኖ አሁን ድረስ አገልግሎት ላይ ይዉላል::
2ኛ - የሄሊኮፕተሩ መጠሪያ - ደንል ሮይቫክ
የተሰራው-በ ደቡብ አፍሪካ ሲሆን “ቀዩ ጭልፊት” በሚል ቅጽል መጠሪያ የሚታወቀው ሄሊኮፕተር ንድፉም ሆነ ሥሪቱ ደቡብ አፍሪካ ነው:: ይህ “ቀዩ ጭልፊት” የተሰኘው ሄሊኮፕተር የመጀመሪያ በረራውን በ1990 እ.ኤ.አ በስኬት ፈፅሟል:: በደቡብ አፍሪካ ጦር ውስጥ የተካተተው በ2011 እ.ኤ.አ ሲሆን እስከ አሁን ድረስም የተመረተቱት 12 ብቻ እንደሆኑ ይነገራል::
1ኛ - የሄሊኮፕተሩ መጠሪያ - ሚልሚ -24
የተሰራው በሶቪየት ሕብረት ሲሆን ሚልሚ - 24 ግዙፍ ከባድ መሣሪያዎችን ይይዛል:: ለመጀመሪያ ጊዜ እ.ኤ.አ በ1972 ለአገልግሎት የበቃ ነው:: እስካሁን ድረስም 2 ሺህ 768 ሄሊኮፕተሮች ተመርተው በተለያዩ ሀገራት አገልግሎት እየሰጡ ነው:: ሚልሚ - 24 በቅጽል መጠሪያው “Flying tank” ወይም በራሪዉ ታንክ በሚል ይታወቃል:: አሁን ላይ 48 ሀገራት እየተገለገሉበት ነው:: ሄሊኮፕተሩን አሜሪካም የምታመርተው ሲሆን በብዛት በማምረት ቻይና ቀዳሚነቱን ይዛለች::
0 Comments