30 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በዓለማችን ለከፋ ርሃብ መጋለጣቸው ተገለጸ፤ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ፣ የአየር ንብረት ቀውስ እና ግጭቶች ተጣምረው የዓለም ርሃብ አስደንጋጭ ደረጃ ላይ መድረሱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) በሪፖርቱ አሳይቷል::

Photo by Guduru Ajay bhargav from Pexels

እንደ ሪፖርቱ ገለፃ አስከፊው ነገር በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ረሃብ 20 በላይ በሆኑ ሀገሮች ሊጨምር ይችላል ሲል የተባበሩት መንግስታት አስጠንቅቋል:: በየመን እና በደቡብ ሱዳን ያሉ ዜጎች ቀድሞውኑ በርሃብ ውስጥ እንደሚገኙ በኤጀንሲዉ የምግብ እና እርሻ ድርጅት (FAO) እና የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) የታተመ አንድ ዘገባ አመልክቷል:: ወደ 34 ሚሊዮን የሚገመቱ ሰዎች በከፍተኛ ርሃብ እንደሚገኙ ተገልጧል:: ይህ ርሃብ በግጭት፣ በአየር ንብረት መዛባት እና በኮቪድ ወረርሽኝ እየተባባሰ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎችም በበረሃ አንበጣ እና አውሎ ነፋስ ምክንያት የተከሰተ ነው::

 

ዶንግዩ የፋኦ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት እንደሚሉትየመከራዉ መጠን በጣም አስፈሪ ነው፤ አሁን እርምጃ መውሰድ እና ህይወትን ለማዳን፣ ኑሮን ለመጠበቅ እና በጣም የከፋ ሁኔታን ለመከላከል ፈጣን እርምጃ መውሰድ የሁላችንም ግዴታ ነው ብለዋል::”

 

ሰሜን ናይጄሪያ፣ መን እና ደቡብ ሱዳን በከፍተኛ የርሃብ አደጋ ዝርዝር ውስጥ እንደሚካተቱ ኤጀንሲዉ አስታውቋል:: በሪፖርቱ ውስጥ ርሃብ ይከሰትባቸዋል ተብሎ የተጠቀሱት አብዛኞቹ ቦታዎች በአፍሪካ የሚገኙ ቢሆኑም የተወሰኑት በአፍጋኒስታን በእስያ፣ በመካከለኛዉ ምስራቅ በሶሪያ፣ ሊባኖስ፣ ላቲን አሜሪካ እና በሃይቲ ጭምር የሚገኙ ናቸው:: “በብዙ ክልሎች የምርት ወቅት ገና ተጀምሯል ወይም ሊጀመር ነው፣ እኛ ከሰዓት ጋር መሮጥ አለብን እናም ይህ እድል የአከባቢን የምግብ ምርት ለመጠበቅ፣ ለማረጋጋት እና ምናልባትም የአከባቢን የምግብ ምርት ከፍ ሊያደርግ ይችላል:: ብለዋል:: በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ፋኦ( FAO) እና የዓለም ምግብ ድርጅት (WFP) ርሃብን ለማስወገድ በምግብ ድጋፍ፣ በጥሬ ገንዘብ እና ለአስቸኳይ መተዳዳሪያቸው አምስት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ዶላር እንዲሰበሰብ ጥሪ አቅርበዋል ተብሏል::

 

በጎረቤታችን በደቡብ ሱዳን በኩል ከሰባት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከሚያዝያ እስከ ሐምሌ ባለው ጊዜ ውስጥ ለከፍተኛ የምግብ ዋስትና እጥረት ይጋለጣሉ ተብሎ እንደሚገመት ሪፖርቱ ያመለከተ ሲሆን 16 ሚሊዮን በላይ የመናዊያን ደግሞ እስከ ሰኔ ወር ድረስ ከፍተኛ የምግብ ዋስትና እጦት ይገጥማቸዋል ተብሎ ይጠበቃል:: ቁጥሩ ካለፈው ዓመት መጨረሻ ጀምሮ የሦስት ሚሊዮን ጭማሪ አሳይቷል::

 

በተለይም ደግሞ የላቲን አሜሪካ በኢኮኖሚ እጅጉን ማሽቆልቆል በጣም የተጎዳው ቀጣና ሲሆን መልሶ ለማገገም በጣም አዝጋሚ እንደሚሆን ሪፖርቱ አመላክቷል:: ሌሎችም እጅግ በጣም የከፋ ረሃብ ያጋጥማቸዋል ከተባሉት ሀገራት መካከል ቡርኪናፋሶ፣ አፍጋኒስታን፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ኢትዮጵያ፣ ሃይቲ፣ ሱዳን እና ሶሪያ በዋናነት ይገኙበታል::