![]() |
| DREAM YOUR BODY – Weight Control With Hypnotherapy |
![]() |
| SOLFEGGIO FREQUENCIES – VOL. 1 |
በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የዓባይ ወንዝን ተከትላ ሱዳንን ግብጽ ቅኝ ገዝታታለች:: እናም አብዛኛዎቹ የአፍሪካ
![]() |
| SOLFEGGIO FREQUENCIES – VOL. 2 |
ሀገራት በወቅቱም ከቅኝ አገዛዝ ነጻ ለመውጣት ሲታገሉ ግብጽ በታላቋ ብሪታንያ ቁጥጥር ሥር ኾና ሱዳንን በባንዳነት ረግጣ አስተዳድራታለች:: ሁለቱ ግብጽና ታላቋ ብሪታንያ በጋራ ኾነው ሱዳንን የገዙት እንደጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር ከ1899 – 1955 ነበር:: ሱዳንም በእንግሊዝ እና በግብጽ ጥምር ቅኝ ግዛት ሥር በነበረችበት ጊዜም ለደረሰባት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፣ ሥቃይና መከራ ሁሉ በዋነኝነት ተጠያቂዋ የአዝንባይ ቅቤ አንጓቿ ግብጽ ናት:: በዚያ ዘመን በደረሰባቸው ግፍ የተነሳ ሱዳናውያንም ማንነታቸውን፣ መንፈሳዊና ቁሳዊ ሀብታቸውን አጥተዋል::
![]() |
| JOURNEY TO SUBCONSCIOUS – 432 Hz MUSIC – VOL. 1: |
ብሔራዊ ጥቅማቸውን ተነጥቀዋል ወይም እንዲረሱ ተገደዋል:: መሬታቸውም በቅኝ ገዢ ባለሀብቶች ተወስዷል:: በወቅቱም ሱዳናውያን የሀገራቸው ባለቤት መሆን አልቻሉም ነበር:: ይህ ሁሉ በደል ሱዳን ላይ ተፈፅሞባት ከቅኝ አገዛዝ መዳፍ ሥር ከወጣች በኋላም ግብጽ የበግ ለምድ ለባሽ ተኩላ ኾና በመቅረብ ለሱዳን ምንም አይነት ክብር ሰጥታ እንደማታወቅ በርካታ የሱዳን የፖለቲካ ልሂቃን የመሰከሩት መራራ ሀቅ ነው::
![]() |
| JOURNEY TO SUBCONSCIOUS – 432 Hz MUSIC – VOL. 2: |
ሁለቱ ግብጽ እና ሱዳን በሚዋሰኑበት ሰሜናዊ
ድንበር
ላይም ግብጽ ትንኮሳ ስትፈጽምባት
ቆይታለች:: ከዚህ በተጨማሪም በተለያየ
ወቅት በሱዳን በተለያዩ ጊዜያት በተደረጉ የመፈንቅለ መንግሥት
ሙከራዎች
የግብጽ እጅ ከጀርባ እንዳለበት
የፖለቲካ ተንታኞች የተስማሙበት ጉዳይ ነው::
እንዲሁም ሱዳን የውስጥ አንደነቷ ተፍረክርኮ
ውስጧ እንዲተረማመስ አማጺ ሚሊሻዎችን በትጥቅና
ሥልጠና በመርዳት ትታወቃለች፡፡ እነዚህ ሁለቱም ሀገራት 1ሺ
200 ኪሎ ሜትር የሚረዝም የጋራ ድንበር አላቸው::
በዚሁ ድንበራቸው መሃል ላይ ከሁለት
ነጥብ አምስት ሚሊዮን
በላይ
የሁለቱ ሀገራት ሕዝብ ይኖራል::
በተለይም የሱዳን ሃሊያብ (Haliyab) ክፍለ ሀገር በማእድን
ሀብት
የበለጸገ ነው:: ይሁንናም ማዕድን አውጪዎች
እና
ተጠቃሚዎቹ የግብጽ ባለሀብቶች በመኾናቸው በእጅ አዙር ቁጥጥር ሥር የወደቀ
በመሆኑ
በይበልጥ ግባፃዊያንን ተጠቃሚ እያደረገ ነው::
የግብጽ ሩጫ ሁሉ በአፍሪካ አንድን አገር በቅንነት ለመርዳት
ሳይኾን በቅንቅንነት ከራሷ ጥቅም
አኳያ ነው:: በየጊዜውም
የእድገት እቅዷን የምታወጣው በሌሎች ሀገራት
ኪሳራ ላይ ተመሥርታም ነው:: ለአብነት ያህል ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር “አለኝ’’
የምትለውን የድንበር ውዝግብ
ለመፍታት
ስትደራደር ከጀርባ እነ ግብጽ መሣሪያ ያስታጥቃሉ፤ ያዘምታሉ፤ ግፋ ወደፊት
በማለት የልብ ልብ በመስጠት ለጥፋት ያጀግናሉ:: ይበጠብጣሉ::
ሱዳን ፤ ግብጽ በምትጎነጉነው በጎነጎነችው
የፖለቲካ ሴራ ምክንያት ከኢትዮጵያን
ጋር በተለያዩ ጊዜያት ግጭት ውስጥ እንድተገባ ሆኗል::
ስለሆነም ግብጽ የራሷ ብሔራዊ ጥቅም እስከተጠበቀ ድረስ የሱዳን ሕዝብ በጦርነት ቢረግፍ የሚደማ
ግድ
አይሰጣትም:: የግብጽ ገዢዎችም ከትላንት
እስከ ዛሬ አቋማቸው በሌሎች ሀገራት
ኪሳራ ሀገራቸው ተጠቃሚ እንድትሆን ማድረግ ነው:: ለአብነት ያህል ግብጽ በታላቁ የዓባይ
ወንዝ ጉዳይ ለመጠቀም ሱዳን ከኢትዮጵያ
ጋር ዐይንና አፈር እንድትኾን ብዙ ለፍታለች::
በሱዳን ኪሳራም ግብጽ ተጠቃሚ መሆን ነው ትልቁ ዓላማዋ ፡፡
ታሪክን ወደ ኋላ መለስ ብለን ስንመለከት እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር በ1960
ግብጽ የአስዋን ግድብ በሱዳን
ድንበር አቅራቢያ ገነባች::
ግድቡም
ተገንብቶ ካበቃ በኋላ የታለቁ ናስር ሐይቅ ውኃ የተንጣለለው በሱዳን ድንበር
ላይ ባለው ሰፊ ቦታ ላይ ነው::
ይህ
ታላቅ ፕሮጄክት ገቢራዊ ሲሆንም
በአካባቢው
የነበረው የሱዳን ኅብረተሰብ ተፈናቅሏል::የግብጽ መንግሥትም ከሁለት መቶ ሺህ በላይ ኅብረተሰብ በማፈናቀል ወደ ኢትዮጵያ
ድንበር ሱዳን እንድታሰፍራቸው የገንዘብ ድጋፍ አድርጋለች::
ታዲያ የሱዳንና ኢትዮጵያን ህዝብ በማተራመስ
ግብጽ ተጠቃሚ እንድትሆን ማድረጓ ከላይ ላነሳነው ሀሳብ አንዱ ማስረጃ ሆኖ መቅረብ ይችላል ፡፡
ስለሆነም ግብጽ፤ ሱዳን ሠላም ውላ ሠላም እንዳታድር አጥብቃ በከፍተኛ ደረጃ ከመስራቷ
በተጨማሪ ሱዳንን ወደ ትንንሽ ሀገራት ለመከፈፋል ያደረገችው
ሴራ ደቡብ ሱዳንን አዲስ
ሀገር ሆና እንድትፈጠር
አስችላለች፡፡ ግብጽ አንዲት ጠንካራ ሱዳንን
ማየት አትፈልግም:: ሆኖም ይህ የግብጽ
መንግሥታት የሴራ የታሪክ
ቅብብሎሽ አሁን ግብጽን እየገዙ እሰከሚገኙት
አብዱለፈታህ አልሲሲ አገዛዝ ዘልቋል:: እንደ አፍሪካ ቀንድ (Horn of Africa) የፖለቲካ ተንታኝ ዶክተር ራሽድ ማፉድ ጥናት ውጤት ግብጽ
ሱዳንን “ይማርሽ ብላ ይውጋሽ”
እንዲሉ
አማጺ ኅይላት አደራጅታ ወደ ሱዳን ልካለች:: ለአብነት ያህል በዳርፉር፣ በደቡብ
ኮርዶፋን፣ በብሉ ናይል ግዛቶች ለሚንቀሳቀሱ ሀይሎች የመሳሪያ
ርዳታ ታደርጋለች:: አማጺያኑ
መሪዎች ከለላ እንደምትሰጣቸው የዶክተር ራሽድ
ማፉድ ጥናት ውጤት መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ሌላው ደግሞ ሱዳን እንደኢትዮጵያ ባሉ ሀገራት ጣልቃ እንድትገባ የማትጎነጉነው የክፋት የፖለቲካ ሴራ የለም::
ይህ ከሱዳን የግዛት
ክልል
ውጪ የምታደርገው መሰሪ ደባዋ ውጤት ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር ገፍታ እንድትገባ አድርጓታልና ነው::
በ2004 ዓ.ም ኢትዮጵያ የታላቁን ዓባይ ወንዝ ላይ ግድብ ስትገነባ የግብጽ ባለስልጣናትን ብስጭት ውስጥ ከቷል:: ሀገሪቱም ዱላዋን በቀጥታ ኢትዮጵያ ላይ ማሳረፍ ስለማትችል በሱዳን
በኩል
አሳርፋለች:: እናም የታላቁን ዓባይ ግድብ (Grand Ethiopian Reinnessance Dam) ከተቻለም ማስቆም ካልተቻለ ደግሞ ማዘግየት የግብጽ ዓላማ ነው::
ይህንን
ዓለማዋን ለማሳካት ኢትዮጵያን በማስጨነቅ በጦርነት ውስጥ ለማስገባት መሞከሯ የሚጠበቅ ነው::
ስለሆነም በአሁኑ ጊዜ ሱዳንና ኢትዮጵያ በድንበር ይገባኛል ምክንያት
የጀመሩትን ግጭት ወደ ለየለት
ጦርነት ውስጥ ለማስገባት
ግብጽ
የማትቆፍረው ጉድጓድ፣ የማትፈነቅለው ድንጋይ የለም:: ይሁንና ኢትዮጵያና ሱዳን በድንበር ይገባኛል ምክንያት ግጭት ውስጥ የገቡት ለብዙ ጊዚያት
ነበር:: ባለፉት መቶ አመታት
በተለያዩ ጊዜያት በድንበር አካባቢ የሚገኙ
የሁለቱ ሀገራት ዜጎች በግጦሽ
እና እርሻ መሬት ይገባኛል አለመግባባት ምክንያት ተጋጭተዋል:: ስለሆነም
በእንዲህ አይነት የተለመዱ ግጭቶች ሁለቱንም
ሀገራት ወደለየለት ጦርነት አይገቡም ባይ ናቸው ምሁሩ:: ሆኖም ግጭቱ
በአሁኑ ጊዜ ለምን ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆነ ብሎ
መጠየቅ ተገቢ ነው::
በአጭሩ ግብጽ የሁለቱን ሀገራት የተለመደ የድንበር
ላይ ግጭት በታላቁ
ዓባይ
ግድብ ግንባታ ላይ ተጽኖ ለመፍጠር በሚያስችላት መንገድ በረቀቀ ዘዴ ለመጠቀም እየሰራች ነው የሚል ይሆናል:: አንዳንድ የሱዳን ወታደራዊ
ሀይል ከፍተኛ የጦር ጄኔራሎችም የግብጽን
ጥቅም ለማስጠበቅ እንደሚሰሩ፣ ከሌሎች የአረብ
ሀገራት መንግስታት ድጋፍ እንደሚደርግላቸው ፖለቲካ ተንታኙ
በጥናት
ወረቀታቸው ላይ ጠቅሰውታል::
“የግብጽ
ስውር አገዛዝ በሱዳን”
በሚል ርእስ በተለያዩ የመገናኛ ብዙኅን
ዘንድ ተኣማኒ መረጃ ይሰጣሉ
በሚል የሚወደሱት ሱዳናዊው
የፖለቲካ
ተንታኝ ሚሰትር ሀቢብ አህመድ
ባሳተሙት
ጽሁፍ ሱዳን ወታደሮቿን ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ያስጠጋችው በግብጽ የዲፕሎማቲክ
ሴራ ትርፍ በማስላት ነው:: በተጨማሪም
በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር የተስተዋለውን የድንበር ላይ ግጭት ተከትሎ ግብጽ ሱዳን ከኢትዮጵያ
ጋር ወደ ለየለት
ጦርነት
እንድትገባ ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገች
ነው::
ግብጽ፤ ኢትዮጵያን
ሕግ የማስከበር ጦርነት ውስጥ
መግባቷን ተገን በማድረግ
[የኢትዮጵያና
ሱዳን] የድንበር ላይ ግጭቱን
ለማባባስ እየሞከረችም ነው:: ግብጽ የሱዳንን ሽግግር
መንግሥት እና ኢትዮጵያ ያለችበትን የፖለቲካ
ሁኔታ ተሞርኩዛ የሱዳንን መንግሥት በፈለገችው
መልኩ እያዘዘችው ትገኛለች:: እናም ግብጽ ፣ ሱዳንና ኢትዮጵያን ወደ ግልጽ
ጦርነት ከአስገባች አካባቢውን
ትርምስ ውስጥ አስገበዋለሁ ብላ ስትራቴጂ
ያወጣች ይመስላል:: የዚህ የለየለት ትርምስ ደግሞ ውጤቱ የናይልን ወንዝ ያለምንም ተቀናቃኝ
የአንበሳውን ድርሻ ለመጠቀም ያስችላታልና ነው::
ኬንያን ሄራልድ
እንደዘገበው ኢትዮጵያ እውነተኛ የሱዳን ጎረቤት
ናት:: የሁለቱ ሀገራት ህዝብ ለዘመናት የቆየ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት
ያላቸው
ናቸው:: ኢትዮጵያውያን የፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ስደተኞች በሱዳን መሬት ላይ እንደሚጠለሉት ሁሉ የሱዳን ስደተኞችም
ኢትዮጵያ ሁለተኛ ቤታቸው ሆና ቆይታለች::
ወደፊትም ይሄው እውነት ይቀጥላል:: ስለሆነም
ሱዳን ከግብጽ ይልቅ ኢትዮጵያ ትበልጥባታለች እንደ ምሁራኑ
አስተያየት::ጊዜያዊ የፖለቲካ ስካሩ ያልፋል::
የሚያዋጣው የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች ዘለቄታዊ
ሕይወት ማሰቡ ነው::
ኢትዮጵያ በሱዳን የሚከሰቱ
የርስበርስ ግጭቶችን ለማብረድ በተባበሩት መንግሥታት
የጸጥታ አስከባሪ ጦር ስር ሆና ወደ ሱዳን መሬት ገባች እንጂ የሱዳንን መሬት ወራ አታቅም:: ኢትዮጵያ የራሷን የማትሰጥ፣ የሰው የማትነካ
ሀገር መሆኗ መታወቅ
አለበት:: ስለሆነም ሱዳን የራሷን
ሉአላዊነት መጠበቅ አለባት እንጂ
በሶስተኛ ወገን ግፊት ከጎረቤቷ ኢትዮጵያ ጋር ግጭት
ውስጥ መግባት የለባትም::
ሱዳን ለሌሎች ሀገራት ጥቅም ብላ ህዝቧን መጉዳትም አይገባም ነበር::
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና የዓባይ
ውኃ
ጉዳይ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ያዕቆብ
አርሳኖ ሱዳን እየሄደችበት ያለው መንገድ
ብሄራዊ ጥቅሟን የሚጎዳ እና ዘላቂ ጥቅሟን የሚያሳጣት እንደሆነ ለአብመድ ተናግረዋል::
ፕሮፌሰር ያእቆብ አክለውም
የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ጉዳይ ሱዳን በመንግስትነት ሳትቋቋም በፊት በኢትዮጵያ እና በቅኝ ገዥዎች መካከል የተጀመረ ነው። ሱዳን የኢትዮጵያን መሬት በኃይል ወስዳ የእኔ ነው ማለት ተቀባይነት የለውም
ብለዋል።
የሰራችው ስህተት
ምንግዜም ቢሆን የሚቆጫት እንደሚሆንም ጠቁመዋል::
ከብዙ አቅጣጫ ሲታይ እና ሲመዘን ሱዳን ዛሬ የድንበር
ጉዳይ የምታነሳበት ወቅት እንዳልሆነ ያመለከቱት
ፕሮፌሰሩ፤ የድንበር ጉዳይ ቢነሳ እንኳ ኢትዮጵያ ውስጥ መሬት አለኝ ብላ በጉልበት ለመውሰድ
የምትንቀሳቀስበትም
ጊዜ አይደለም ብለዋል:: ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ረጅም ድንበር ትጋራለች:: የሀገራቱ ሕዝቦችም ለአያሌ ዓመታት በሠላም
አብረው የኖሩ ናቸው::ይህ እውነታ በተጨባጭ ባለበት
እንደ አለመታደል ሆኖ የሱዳን መንግስት
ለራሱ እና ለሕዝቡ በማይጠቅም መንገድ
እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ፕሮፌሰሩ አስታውቀዋል።
የሱዳን መሪዎች
የአካባቢውን ሰላም፣ ልማት እና ጸጥታ በሚጎዳ መንገድ መራመድ የመጀመሪያቸው እንዳልሆነ
የጠቆሙት
ፕርፌሰሩ፣ አሁን ግን እጅግ በጣም ተለዋዋጭ በሆነና ለሱዳን ህዝብ በማይጠቅም፣ አካባቢውን ወደ ውዝግብ
በሚወስድ መንገድ ውስጥ መግባቱን አመልክተዋል::
ፕሮፌሰር ያዕቆብ
አርሳኖ እንደገለጹት ሱዳን ላይ የመጡ መንግሥታት ብሄራዊ ጥቅማቸውን ከማስከበር ይልቅ የሦስተኝ ወገንን አጀንዳ እየተገበሩ ነው::
በመሆኑም ሥራቸው ሁሉ በሀገራቱ
ሕዝቦች መካከል ያለውን ጉርብትና እና ወንድማማችነት የሚመጥን አይደለም:: አሁን ሱዳን እየሄደችበት
ያለው
መንገድና የያዘችው አቋም ብሄራዊ
እና ዘላቂ ጥቅሟንም የሚያሳጣ ነው::
ስለዚህ የሱዳን መንግሥት የፖለቲካ ውሳኔውን
መለስ ብሎ መፈተሽ አለበት::






1 Comments
intersting
ReplyDelete