ጥቂት ስለ ደጃዝማች በቀለ ወያ
ደጃዝማች በቀለ ወያ ከእናታቸው ወይዘሮ ብርቄ
ጅሎ እና ከአባታቸው
አቶ ወያ ኦቢሴ ነሐሴ
21 ቀን 1902 ዓ.ም በደቡብ
ሸዋ ሶዶ ተወለዱ፡፡ አጎታቸው ደጃዝማች
ገብረማርያም
ዘንድ በመሄድም ፈረስ ግልቢያ
እና ኢላማ ተኩስ ከፍ ሲሉም የአስተዳደር ትምህርት እየተማሩ አደጉ። በመቀጠልም አጎታቸውን
ተከትለው
ወደ አዲስ አበባ በማቅናት
የታንክ መስበሪያ ስልጠናን ወሰዱ፡፡ ከዚህም
በኋላ ፋሺሽት ኢጣሊያ ሀገራችንን በወረረ
ጊዜ ደጃዝማች በቀለ ወያ ከአጎታቸው
ገብረማርያም ጎን ተሰልፈው ለእናት ሀገራቸው
ትግል ጀመሩ፡፡ ከአጎታቸው ጋር ሆነው በተዋጉባቸው ጦርነቶችም ከ17 በላይ የጠላት ታንኮችን አወደሙ፡፡ የካቲት 13 ቀን
1929 ዓ.ም በተደረገ ከባድ ውጊያ ላይ ደጃዝማች በቀለ ወያ
አጎታቸውን በሞት በማጣታቸው
ጦሩን
የመምራት ኃላፊነት ወደ እሳቸው
ዞረ ፡፡
ደጀዝማች በቀለ ከተለያዩ አርበኞች ጋር ግንኙነት
በመፍጠር፤ ከጀግናው አርበኛ
ገረሱ
ዱኪ ጋር በመቀናጀት፤ ከነራስ
አበበ አረጋይ ጋር በመመካከር የጠላት
ኢጣሊያን ጦር መግቢያ መውጫ
አሳጡት፡፡ የፋሺስት ኢጣሊያ
ጦርም
በተደጋጋሚ ደጃዝማች በቀለን እጃቸውን እንዲሰጡ ቢጠይቅም
እሳቸው ግን “ነፃነት ወይንም ሞት” የሚል መልስ በመስጠት ውጊያቸውን ቀጠሉ፡፡
በተሳተፉበትም
ውጊያ በሙሉ በርካታ የጠላት
መኮንኖችንና
ወታደሮችን የገደሉ፣ ብዙ ታንኮችን
ያወደሙ
ጀግና አርበኛ ነበሩ፡፡
ስለጀግንነታቸውም፦
“የበቀለ ፈረስ ክንፍ የለው እንዲያው ይከንፋል፤
እሳተ ገሞራ ከጉያው
ይተፋል።
ልጁ በቀለ አባቱ ወያ፤
አጋድሞ ባረከው ነጩን አህያ።”
ተብሎላቸዋል።
የጠላት ፋሺስት
ጦር ከሀገራችን ከተባረረ በኋላም ደጀዝማች
በቀለ ወያ በተለያዩ ክልሎች ላይ በመሾም በአስተዳዳሪነት ሲያገለግሉ ቆይተው በሚያዚያ
6 ቀን 1946 ዓ.ም ባደረባቸው
ሕመም ምክንያት ከዚህ ዓለም
በሞት ተለይተዋል፡፡ ደጃዝማች በቀለ ወያ
በሁሉ ዘንድ የሚወደዱና
የሚከበሩ፤
ለሁሉ አዛኝና ለሀገራቸው ታማኝ የነበሩ በመሆናቸው በሞታቸው ጊዜ
“በቀለ በነሐሴ በሚያዚያ
ታጨደ
ስመ ጥሩው ጀግና ያለጊዜው ሄደ”
ተብሎ ገና በ44 ዓመታቸው በማለፋቸው ተገጥሞላቸው ነበር፡፡
ደጃዝማች በቀለ ወያ ከጠላት ጋር ሲዋጉ በ 5 ጥይቶች ቆስለው ስለነበር እና ጥይቶችም ያለወጡላቸው በመሆኑ
እያደር ወደ ከፍተኛ ህመም አድጎ በዛም ላይ የጉበት በሽታ ታመው ስለነበር የሀገር ውስጥ ህክምና ሊያድናቸው አልቻለም፡፡ በመጨረሻም
በቀዳማዊ ሐይለስላሴ ትዕዛዝ ሚያዚያ 5 ቀን 1946 ዓ.ም ወደ ሲዊዘርላንድ
ጉዞ ጀምረው በአውሮፕላን ላይ በመድከማቸው በቂ ህክምና ሳያገኙ ከዚህ አለም በሞት ተለይተው አስከሬናቸው ወደ ሀገር ተመልሶ ሚያዚያ
10 ቀን 1946 ዓ.ም በቅድስት ሥላሴ ቤተ-ክርስቲያን ቀብራቸው እንደተፈፀመ የታሪክ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡
0 Comments